ቀጥታ፡

ቱርክዬ ርዕደ-መሬት ባጋጠማት ወቅት ኢትዮጵያ ላሳየችው አጋርነት ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን ምስጋና አቀረቡ

አዲስ አበባ ሚያዝያ 18/2015(ኢዜአ)፦ቱርክዬ ርዕደ-መሬት ባጋጠማት ወቅት ኢትዮጵያ ላሳየችው አጋርነት ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን ምስጋና አቀረቡ።

የቱርኪዬ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን በሀገሪቱ በርዕደ-መሬት አደጋ ወቅት ድጋፍ ላደረጉ አገራት የሜዳሊያ እና የምስጋና ምስክር ወረቀት አበርክተዋል።

በመርሐ-ግብሩ ፕሬዝዳንት ኤርዶኻን የኢትዮጵያ መንግስት በአገሪቱ ተከስቶ በነበረው የርዕደ-መሬት አደጋ ወቅት ላደረጉት አፋጣኝ የነፍስ አድን ድጋፍ እና ትብብር ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።


 

ፕሬዝዳንቱ በቱርክዬ የኢትዮጵያ አምባሳደር ለሆኑት አደም መሐመድ እና ለኢትዮጵያ የነፍስ አድን ቡድን መሪ ሌ/ጄኔራል ደስታ አቢቼ የሜዳሊያ እና የምስጋና ምስክር ወረቀት አበርክተዋል።

 

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም