ቀጥታ፡

አገራዊ ለውጡን ተከትሎ የኢትዮጵያን ከፍታ የሚመጥንና ትውልድን የሚያኮራ አየር ሃይል መገንባት ተችሏል - ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

አዲስ አበባ ሚያዚያ 17/2015(ኢዜአ)፡- አገራዊ ለውጡን ተከትሎ የኢትዮጵያን ከፍታ የሚመጥንና ትውልድን የሚያኮራ አየር ሃይል መገንባት ተችሏል ሲሉ የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ።

"ሰማዩ የእኛ ነው" የተሰኘና በኢፌዴሪ አየር ሃይል የተከናወኑ የለውጥ ስራዎችን የሚያስቃኝ ዘጋቢ ፊልም ለእይታ ቀርቧል።

በኢፌዴሪ አየር ሃይል ገቢ ውስጥ በተከናወነው ምረቃ መርሃ ግብር ላይ የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ሌሎች ከፍተኛ የጦር መኮንኖችና ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።


 

ዘጋቢ ፊልሙ አገራዊ ለውጡን ተከትሎ ባለፉት አራት ዓመታት በኢፌዲሪ አየር ሃይል የተከናወኑ የለውጥ ስራዎችን የሚያስቃኝ ነው።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንዳሉት፣ የኢትዮጵያ አየር ሃይል በምስረታው በአፍሪካ ቀደምት ታሪክ ያለው ነው።

ነገር ግን የእድሜውን ያህል በሚፈለገው ከፍታ ላይ እንዳልነበር አስታውሰዋል።

አገራዊ ለውጡን ተከትሎም አየር ሃይሉን በሰው ሃይል፣ ትጥቅና ምቹ የስራ ከባቢ ማደራጀት መቻሉን ተናግረዋል።

በመሆኑም አሁን ላይ የኢትዮጵያን ከፍታ የሚመጥንና ትውልድን የሚያኮራ አየር ሃይል መገንባት ተችሏል ነው ያሉት።

የኢፌዴሪ አየር ሃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ በበኩላቸው አየር ሃይሉ አሁን ላይ ወቅቱን በሚመጥን ዘመናዊ ትጥቅ መደረጃቱን ጠቅሰዋል።


 

የሰው ሃይል አደረጃጀቱም እጅግ የተጠናከረ መሆኑን እንዲሁ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም