የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው
አዲስ አበባ ሚያዝያ 17/2015(ኢዜአ):- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡
ምክር ቤቱ በጉባኤው ለውይይት የያዛቸው አጀንዳዎች፡-
1.በምክር ቤቱ የአሰራርና የአባላት ስነ-ምግባር ደንብ አንቀፅ 92 መሰረት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች የሚሰጡትን መልስ ማዳመጥ፣
2.የመከላከያ ሰራዊት አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ማጽደቅ፣
3.የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ የፕላን በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ አዋጁን ማጽደቅ፣
4.የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 1151/2011ን ለማሻሻል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት እንዲሁም የአገር መከላከያ ሠራዊት አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ እና የኤክሳይስ ታክስን ለማሻሻል የቀረበ ረቂቅ አዋጅን ማጽደቅ መሆኑን ምክር ቤቱ በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ ገልጿል።