ቀጥታ፡

በተጠባቂው የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ቅዱስ ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማን አሸነፈ

አዲስ አበባ ሚያዚያ 14/2015(ኢዜአ)፦ በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ20ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ፋሲል ከነማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቶጎዋዊው አጥቂ እስማኤል ኦሮ-አጎሮ በ71ኛው ደቂቃ ላይ ያስቆጠራት ግብ ቅዱስ ጊዮርጊስ በዋንጫ ፉክክሩ ወሳኝ ሶስት ነጥብ እንዲያገኝ አስችሎታል።

የፊት መስመር ተጨዋቹ በሊጉ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ 19 ከፍ በማድረግ የከፍተኛ ግብ አስቆጣሪነት መሪነቱን አጠናክሯል።

ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ ነጥቡን ወደ 45 ከፍ ያደረገ ሲሆን ፋሲል ከነማ በ27 ነጥብ በነበረበት 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

የሁለቱን ክለቦች ጨዋታ በርካታ የቡድኖቹ ደጋፊዎች በስታዲየሙ በመገኘት ተከታትለውታል።

በ20ኛ ሳምንት የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ-ግብር የመጨረሻ ጨዋታ በድሬዳዋ ከተማና ሀዋሳ ከተማ መካከል ከምሽቱ 12 ሰአት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም