የጄኔራል ሰዓረ መኮንን መታሰቢያ ፓርክና ሐውልት ተመረቀ - ኢዜአ አማርኛ
የጄኔራል ሰዓረ መኮንን መታሰቢያ ፓርክና ሐውልት ተመረቀ
አዲስ አበባ ሚያዝያ 14/2015(ኢዜአ)፦የቀድሞ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን መታሰቢያ ፓርክና ሐውልት ዛሬ በአዲስ አበባ ተመረቀ።
በምርቃቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይ፣ ጄኔራል መኮንኖች፣ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኃላፊዎች፣ የጄኔራል ሰዓረ መኮንን ቤተሰቦችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።
ሐውልቱ በአዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ አካባቢ በስማቸው በተሰየመ ፓርክ ውስጥ ክብራቸውን በሚመጥን መልኩ ተገንብቶ ለምርቃት መብቃቱ ተገልጿል።
የቀድሞ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጄኔራል ሰዓረ መኮንን አገር ወዳድ የኢትዮጵያ ልጅ ነበሩ።
ጄኔራል ሰዓረ ከግንቦት 2010 ዓ.ም ሕይወታቸው እስካለፈበት ሰኔ 15/2011 ዓ.ም ድረስ የኢፌዴሪ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም በመሆን ኢትዮጵያን በታላቅ ታማኝነትና ቅንነት አገልግለዋል።