ቀጥታ፡

1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሶላትና ሌሎች ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች በአዲስ አበባ ስታዲየም በድምቀት ተከበረ 

 አዲስ አበባ  ሚያዝያ  13/2015 (ኢዜአ)1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሶላትና በሌሎች ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች በአዲስ አበባ ስታዲየም በድምቀት ተከብሯል።

በስነስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼኽ ሀጅ ኢብራሂም ቱፋን ጨምሮ የእምነቱ አባቶች እና ተከታዮች  ተገኝተዋል።

በዓሉን በማስመልከትም የዒድ አልፈጥር በዓል የጀመዓ ሶላት በድምቀት ተከናውኗል።

የሶላት ስነስርዓቱ መጠናቀቁን ተከትሎ የእምነቱ ተከታዮች የዒድ አልፈጥር በዓልን በ ”ዘካ ተልፊጥር” ከተቸገሩ ወገኖች ጋር ማዕድ በመጋራት እና በማገዝ እንደሚያከብሩም ተገልጿል።

በስነስርዓቱ ላይ ሁሉም ሰላምን፣ አብሮነትን እና መረዳዳትን እንዲያጠናክር ሃይማኖታዊ መልዕክቶች ተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም