ቀጥታ፡

ጨረቃ ዛሬ ሀሙስ በመታየቷ 1ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል ነገ አርብ ይከበራል

 

አዲስ አበባ ሚያዚያ 12/2015(ኢዜአ):- ጨረቃ ዛሬ ሀሙስ በመታየቷ 1ሺህ 444ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል ነገ አርብ እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታወቀ።

በዓሉ ነገ የሚከበረው የሻዋል ወር ጨረቃ ዛሬ በመታየቷ እንደሆነም ጠቅላይ ምክር ቤቱ ገልጿል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት ሸህ ሐጂ ኢብራሂም ቱፋ የኢድ አል ፈጥር በዓል አስመልክቶ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ሕዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ሲያከብር በችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በመደገፍ ሊሆን እንደሚገባ አመልክተዋል።

በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የመተዛዘንና የመረዳዳት እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም