ቀጥታ፡

የጉምሩክ ኮሚሽን እና ኢትዮ ቴሌኮም የቀረጥና የግብር  ክፍያን  በቴሌብር መሰብሰብ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ 

 አዲስ አበባ ሚያዝያ 12 / 2015(ኢዜአ) ፡የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን እና ኢትዮ ቴሌኮም የጉምሩክ ቀረጥና የግብር  ክፍያን  በቴሌብር በቀላሉ መሰብሰብ የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ።

የስምምነት የፊርማውን የኢትዮ ቴሌኮም  ዋና ሥራ አሥፈፃሚ  ፍሬህይወት ታምሩ እና የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ተፈራርመዋል።

የኢትዮ ቴሌኮም  ዋና ሥራ አሥፈፃሚ  ፍሬህይወት ታምሩ በዚህ ወቅት እንደገለፁት፤ የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ለማሳለጥ ጊዜና ወጪ ቆጣቢ የሆነ አሰራር እየተዘረጋ ነው።

በዛሬው ዕለት የጉምሩክ አሰራርን፣ የቀረጥና የግብር ክፍያዎችን በቴሌብር ለማከናወን የተፈረመው ስምምነትም የዚሁ የዲጂታል ኢኮኖሚ ስርዓት አካል ነው ብለዋል።


 

የጉምሩክ ኮሚሽን ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ በበኩላቸው ኮሚሽኑ የሚያከናውናቸውን ተግባራት በቴክኖሎጂ በማስደገፍ ዜጎች ቀልጣፋ አገልግሎት እንዲያገኙ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ለዚህም ደንበኞች የጉምሩክ ቀረጥና ግብር ክፍያን በቴሌብር እንዲፈፅሙ የሚያሰችል ስምምነት ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር መፈረሙን በማንሳት።

ስምምነቱ መንግስት የቀረጥና የግብር ገቢን በወቅቱ እንዲሰበስብ ያስችላል ያሉት ኮሚሽነሩ ተገልጋዮች ክፍያቸውን በወቅቱና ያለምንም የጊዜ ብክነት እንዲከፍሉ ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥር ገልጸዋል።

 

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም