ቀጥታ፡

መንግስት በሱዳን የዜጎቻችንን ሁኔታ እየተከታተለ ነው--የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ሚያዝያ 12/2015(ኢዜአ)፦ መንግስት በሱዳን የሚገኙ ዜጎቻችንን ሁኔታ እየተከታተለ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሱዳን ካለው ወቅታዊ የፀጥታ ሁኔታ አንፃር የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዜጎቻችንን ሁኔታ በቅርብ እየተከታተለ ነው፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዋናው መስሪያ ቤት እና ካርቱም በሚገኘው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ኤምባሲ አማካኝነት የዜጎቻችንን ደህንነት ለመጠበቅ እየሰራ ይገኛል፡፡

የሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶችና አጎራባች ክልሎች አባል የሆኑበት ግብረ-ኃይል በአገር አቀፍ ደረጃ ተቋቁሟል ያለው ሚኒስቴሩ አስፈላጊ መረጃዎችን በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም