ቀጥታ፡

የገንዘብ ሚኒስቴርና የፈረንሳይ ኤምባሲ የኢኮኖሚ ኮሚቴዎች የውይይት መድረክ ተጀመረ

አዲስ አበባ ሚያዝያ 11/2015(ኢዜአ)፦ ሶስተኛው የገንዘብ ሚኒስቴር እና የፈረንሳይ ኤምባሲ የኢኮኖሚ ኮሚቴዎች ውይይት በአዲስ አበባ ተጀምሯል፡፡ 

በመድረኩ የኢትዮጵያ እና የፈረንሳይ የፋይናንስ ባለሙያዎች፣ የስራ ሃላፊዎች እና የፈረንሳይ ኩባንያ ተወካዮች እየተሳተፉ ነው፡፡

በውይይት መድረኩ የፈረንሳይ ኩባንዎች የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ እድገት ሊደገፉ በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር እንደሚደረግ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም በታዳሽ ሀይል ዘርፍ ያሉ የኢንቨስትመንት ተግዳሮቶች እና መፍትሄዎቻቸውን በተመለከት ውይይት ይደረጋል፡፡

በመድረኩ የተለያዩ ኩባንያዎች ሃላፊዎች ተጋብዘው ተሞክሮዎቻቸውን  እንደሚያቀርቡ ከፈረንሳይ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም