የኢትዮጵያ የፋይናንስ ልዑክ ከዓለም ባንክና አይ ኤም ኤፍ ሃላፊዎች ጋር ሲያደርግ የቆየው ውይይት ተጠናቀቀ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ የፋይናንስ ልዑክ ከዓለም ባንክና አይ ኤም ኤፍ ሃላፊዎች ጋር ሲያደርግ የቆየው ውይይት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ ሚያዝያ 9/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ልዑክ ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) ሃላፊዎች ጋር ለአንድ ሳምንት ሲያደርግ የቆየውን ውይይት አጠናቋል፡፡
በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ እና በብሄራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ የተመራው ልዑክ ከዓለም ባንክ እና ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(አይ ኤም ኤፍ) ዳይሬክተሮች ጋር ሲያደርግ የነበረው ውይይት ተጠናቋል፡፡
የፋይናንስ ልዑኩ በቆይታው ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም(አይ ኤም ኤፍ) ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጆርጂየቫ እና ልዑካቸው ጋር ምክክር ማድረጉን አንስተዋል፡፡
የተደረገው ውይይት ኢትዮጵያ የሚያስፈልጋትን የልማትና ሰብዓዊ ድጋፍ ለማግኘት የሚያስችል መሆኑን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር (ዶክተር/ኢንጂነር) ስለሺ በቀለ በትዊተር ገጻቸው ጠቁመዋል፡፡