ቀጥታ፡

የኢጣሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ ሚያዝያ 7/2015(ኢዜአ)፦ የኢጣሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በኢትዮጵያ የነበራቸውን ይፋዊ የስራ ጉብኝት አጠናቀው ወደ ሀገራቸው ተመለሱ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኀላፊዎች በቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው ሸኝተዋቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በኢትዮጵያ በነበራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር የሁለቱን አገራት ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ካደረጉት የኢጣሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ እና ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ ጋር ፍሬያማ እና ውጤት ተኮር የሦስትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን ገልፀዋል።

የኢትዮጵያ፣ ጣልያን እና ሶማሊያ ሀገራት መሪዎች የሶስትዮሽና ባለብዙ ወገን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ስለመስማማታቸው መዘገባችን ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም