የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼህ መሀመድ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ ሚያዝያ 6/2015(ኢዜአ)፦ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼህ መሀመድ አዲስ አበባ ገብተዋል።


 

ፕሬዝዳንቱ ቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ አደም ፋራህ አቀባበል አድርገውላቸዋል።


 

በአቀባበል ስነ ስርአቱ ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ተገኝተዋል።


 

ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼህ መሀመድ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ የሁለቱን አገራት ግንኙነት በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ ውይይት ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም