የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ - ኢዜአ አማርኛ
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ ሚያዝያ 6/2015(ኢዜአ):-የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሯ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ጆርጂያ ሜሎኒ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው የሁለት ቀናት የስራ ቆይታ ከመንግስትና ከአፍሪካ ሕብረት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የሚኒስትሯ ጉብኝት ጣሊያን ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ሰብዓዊና የልማት ድጋፍ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ለመምክር እንደሚሆንም ተጠቁሟል።
ጉብኝቱ የኢትዮጵያ እና የጣሊያንን አጋርነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ኢትዮጵያና ጣሊያን በሚጋሯቸው ቀጣናዊ፣ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት እንደሚያደርጉም ተጠቅሷል።