የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ አድባራት እየተከበረ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ አድባራት እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ ሚያዝያ 6/2015(ኢዜአ)፦ የስቅለት በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ አድባራት በጸሎት እና በስግደት እየተከበረ ይገኛል።
በቤተ ክርስቲያኗ የስቅለት በዓል ሥርዓት በድምቀት ከሚከበርባቸው አብያተ ክርስቲያናት መካከል መንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ትገኝበታለች።
በገዳሟ እየተከበረ በሚገኘው የስቅለት በዓል ሥርዓት ላይ የእምነቱ ተከታዮች እየተሳተፉ ነው።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዘንድ በሰሙነ ህማማት እለት አርብ የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለትን በየአጥቢያ ቤተክርስቲያናት የእምነቱ ተከታዮች በድምቀት ያከብሩታል።
እለተ አርብም የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት የሚታሰብበት ቀን ሲሆን ኢየሱስ ክርስቶስ በእለተ አርብ ያያቸው የስቃይና የመከራ ጊዜያት ስለፍፁም ፍቅር ሲል እንደሆነ ይታመናል።
በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በድምቀት እየተከበረ በሚገኘው የስቅለት በዓል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ፓትሪያርክ ብፁዕ ወቅዱስ ቀዳማዊ አቡነ ማቲያስ፣ ሊቀጳጳሳት፣ አባቶች እና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።