የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል እየተከበረ ነው

 

አዲስ አበባ ሚያዝያ 6/2015(ኢዜአ):-የኢየሱስ ክርስቶስ የስቅለት በዓል በመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በመከበር ላይ ይገኛል።

በዓሉ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያንና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ሕብረት በስግደት፣ በጾም፣ በጸሎትና በዝማሬ እየተከበረ ነው ያለው።

ዕለተ አርብ በክርስትያኖች ዘንድ ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀራንዮ አደባባይ ተሰቅሎ መዋሉ የሚታሰብበት ቀን ነው።

በዕለቱ ቀኑን የሚያወሱ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍሎች ይነበባሉ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ደግሞ በ3፣ በ6 እና በ9 ሰዓትም በዕለተ ስቅለት የተከናወኑ ተግባራት እየታሰበ ይሰገዳል።

የጸሎተ ሐሙስ መታሰቢያ ስነ-ሥርዓት ትናንት በድምቀት መከበሩ ይታወቃል።

 

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም