ቀጥታ፡

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትን አመሰገነ

አዲስ አበባ ሚያዚያ 5/2015(ኢዜአ)፦ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ለገበታ ለትውልድ ፕሮጀክት የተለያየ የገንዘብ መጠን ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትን አመሰገነ።

ጽህፈት ቤቱ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ "የገበታ ለትውልድን ጥሪ ተቀብላችሁ ኃላፊነት ስለወሰዳችሁ፤ ለመጪው ትውልድ የምትመጥን ኢትዮጵያን ለመገንባት የድርሻችሁን ስላዋጣችሁ እናመሰግናለን" ብሏል።

ጽሕፈት ቤቱ በሰባተኛ ዙር ይፋ ያደረጋቸው ተቋማት ዝርዝር አሊ ጃማ አህመድ (ዳሃብሺል) ቃል ከገባው 20 ሚሊዮን ብር ላይ 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ገቢ ማድረጉን ገልጿል።

በተጨማሪም ዥን ዥን የብረታ ብረት ኢንዱስትሪ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ማህቪር ኢንዱስትሪስ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ጄይ ጄይ ጨርቃጨርቅ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ዋሽንግተን የጤና ማዕከል ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ኤ ጂ ፒ ፖልትሪ ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር፣ ኢስት ስቲል ሀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር እያንዳንዳቸው ቃል የገቡትን 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ገቢ ማድረጋቸውን ጽህፈት ቤቱ አስታውቋል።

የምሩ ነጋ 12 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባቱን እንዲሁም መኪያ ኢንተርፕራይዝ፣ ሮሚና፣ ቢ ኤን ቲ፣ አብርሃም አበበ፣ አለማየሁ ከተማ፣ ገምሹ በየነ፣ ጌቱ ገለቴ እና ሱሁራ የተባሉ ባለሀብቶች እና ድርጅቶች እያንዳንዳቸው 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸውን ጽህፈት ቤቱ ባወጣው መረጃ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም