ቀጥታ፡

አምባሳደር ተፈራ ደርበው የኢትዮጵያን  የኢንቨስትመንት አማራጮች ለቻይና የአፍሪካ ልማት ፈንድ ዋና ስራ አስፈፃሚ  ገለጻ አደረጉ

አዲስ አበባ ሚያዝያ 5/2015(ኢዜአ)፦ አምባሳደር ተፈራ ደርበው በኢትዮጵያ በሚካሄደው የኢንቨስትመንት ፎረም እና በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ለቻይና የአፍሪካ ልማት ፈንድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሺ ዌንጁ ገለጻ አደረጉ።

በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከቻይና የአፍሪካ ልማት ፈንድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሺ ዌንጁ ጋር በኢንቨስትመንት አማራጮች ዚሪያ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በኢትዮጵያ በሚካሄደው የኢንቨስትመንት ፎረም እና በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ አምባሳደር ተፈራ ገለጻ አድርገዋል።

የቻይና የአፍሪካ ልማት ፈንድ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሺ ዌንጁ በበኩላቸው የቻይና የአፍሪካ ልማት ፈንድ በአፍሪካ ኢንቨስት በማድረግ እና የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስተዋወቅ ረገድ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የቻይና ልማት ፈንድ በመጭው ሰኔ ወር በሚያዘጋጀው የቻይና-አፍሪካ የፋይናንስ እና ኢንቨስትመንት ሲምፖዚየም ላይ አምባሳደር ተፈራ እንዲሳተፉ መጋብዛቸውን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም