ቀጥታ፡

በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ሀላፊዎች ጋር ተወያየ

 

አዲስ አበባ ሚያዝያ 3/2015(ኢዜአ) በገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሺዴ የተመራ ልዑክ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች ጋር መወያየቱ ተገለጸ።

ውይይቱ ከፀደይ ወቅት ስብሰባ ጎን ለጎን የተካሄደ ሲሆን ከዓለም ባንክ፣ ከዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይ ኤም ኤፍ) እና ከዓለም አቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን (አይ ኤፍ ሲ) ፕሬዚዳንቶች እና ዳይሬክተሮች ጋር መደረጉ ተገልጿል።


 

በውይይቱ አቶ አህመድ ሺዴን ጨምሮ የብሔራዊ ባንክ ዋና ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ተሳትፈዋል።

የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታዎች፣ ምጣኔ ሀብት፣ ፋይናንስ እና አጋርነትን በተመለከተ ለኢትዮጵያ ልማት ጠቃሚ በሆኑ ጉዳዮች ዙሪያ ገለፃ መቅረቡም ተመላክቷል።

በአቶ አህመድ ሺዴ የተመራው ልዑክ ጠቃሚ ውይይት ማድረጉን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) በይፋዊ  ማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስታውቀዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም