በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ድሬዳዋ ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን አሸነፈ
አዲስ አበባ ሚያዚያ 2/2015 (ኢዜአ)፦ በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ18ኛ ሳምንት መርሐግብር ድሬዳዋ ከተማ ሀዲያ ሆሳዕናን 2 ለ 1 አሸንፏል።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጋናዊው አጥቂ ሪችሞንድ ኦዶንጎ በ43ኛው ደቂቃ ያስቆጠራት ግብ ሀድያ ሆሳዕናን መሪ አድርጎ ነበር።
ይሁንና ድሬዳዋ ከተማ ቢኒያም ጌታቸው በ50ኛው እንዲሁም አቤል አሰበ በ68ኛው ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ግቦች አሸናፊ ሆኗል።
ቢኒያም ጌታቸው በሊጉ ያስቆጠራቸውን ግቦች ወደ 10 ከፍ ማድረግ ችሏል።
ውጤቱንም ተከትሎ ድሬዳዋ ከተማ ነጥቡን ወደ 24 ከፍ በማሳደግ ከነበረበት 11ኛ ወደ 8ኛ ደረጃ ከፍ ብሏል።
በአንጻሩ ሀዲያ ሆሳዕና በ24 ነጥብ በነበረበት 7ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ18ኛ ሳምንት መርሐግብር የመጨረሻ ጨዋታ ከምሽቱ 12 ሰአት ላይ በለገጣፎ ለገዳዲና ኢትዮጵያ መድን መካከል በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ይደረጋል።