ቀጥታ፡

ዋሊያዎቹ ወደ አሜሪካ ሊጓዙ ነው

 

አዲስ አበባ ሚያዝያ 2/ 2015 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን እ.አ.አ ሐምሌ 2023 ወደ አሜሪካ እንደሚያቀና ተገለጸ።

ቡድኑ በአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲና አትላንታ በሚኖረው የጉብኝት ጉዞ የወዳጅነት ጨዋታዎችን እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

እ.አ.አ ሐምሌ 8 ቀን 2023 ብሔራዊ ቡድኑ ከካሪቢያን አገራት ብሔራዊ ቡድኖች ጋር እንደሚጫወት አመልክቷል።

ጉዞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ያላቸውን ክህሎትና ብቃት ለማሳየት እድል እንደሚፈጥርላቸው ፌዴሬሽኑ ገልጿል።

የትኬትና የመጫወቻ ሜዳዎች የተመለከቱ መረጃዎች በቅርቡ እንደሚገለጹ ጠቁሟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም