"ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023" ዓመታዊ የኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
"ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023" ዓመታዊ የኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ ይካሄዳል
አዲስ አበባ ሚያዝያ 2/2015(ኢዜአ):- "ኢንቨስት ኢትዮጵያ 2023” ዓመታዊ የኢንቨስትመንት ፎረም ከሚያዚያ 18 እስከ 20/2015 ዓ.ም ድረስ በአዲስ አበባ ስካይ ላይት ሆቴል ይካሄዳል።
የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ተመስገን ጥላሁን ፎረሙን በማስመልከት ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
የኢንቨስትመንት ፎረሙ አላማ ኢትዮጵያ ያላትን የኢንቨስትመንት አማራጮች ለዓለም አቀፍ ባለሀብቶች ማስተዋወቅ መሆኑን ገልጸዋል።
በፎረሙ ላይ ከ600 በላይ የውጭ ባለሀብቶች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅም አቶ ተመስገን ገልጸዋል።
በፎረሙ ላይ የፌዴራል፣ የክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች የሚገኙ በመሆኑ የኢንቨስትመንት አማራጮችና ማብራሪያ ይሰጣሉ ብለዋል።
ፎረሙ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ኮሚሽኑ በመግለጫው አስታውቋል።