በጋምቤላ ክልል በመንግስት የተጠናው የልዩ ኃይል አደረጃጀታዊ መዋቅርን የማስፈጸም ተግባራዊ ስራ ተጀምሯል--የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን - ኢዜአ አማርኛ
በጋምቤላ ክልል በመንግስት የተጠናው የልዩ ኃይል አደረጃጀታዊ መዋቅርን የማስፈጸም ተግባራዊ ስራ ተጀምሯል--የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን
ጋምቤላ ሚያዝያ 1/2015(ኢዜአ)፦በጋምቤላ ክልል በመንግስት የተጠናው የልዩ ኃይል አደረጃጀታዊ መዋቅርን የማስፈጸም ተግባራዊ ስራ መጀመሩን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሰናይ አኩዎር የልዩ ኃይል አደረጃጀቱን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት በመንግስት የተጠናውን አዲሱን የልዩ ኃይል አደረጃጀት ተግባራዊ የማድረግ ስራ ተጀምሯል።
በአሁኑ ወቅት የክልሉ ልዩ ኃይል አባላት በሚፈልጉት የጸጥታ መዋቅር ለመደራጀት ምዝገባ እያካሄዱ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ከክልልና ከፌዴራል የጸጥታ አካላት የተውጣጣ ኮሚቴ ተቋቁሞ የልዩ ኃይል አባላት ወደሚፈልጉት የፖሊስና የሀገር መከላከያ ሰራዊት መዋቅሮች የማደራጀት ስራ እየተሰራ ነው ብለዋል።
አደረጃጀቱ የጸጥታ መዋቅሩን ይበልጥ የሚያጠናክረው በመሆኑ የክልሉ መንግስት በሙሉ ልብ ተቀብሎ ለተግባራዊነቱ በትኩረት እየሰራ መሆኑንም ኮሚሽነር ሰናይ አስታውቀዋል።