ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ወታደራዊ  አካዳሚ ያሰለጠናቸውን እጩ መኮንኖች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት እያስመረቀ ነው 

ሀረር መጋቢት 30 /2015(ኢዜአ) ፡-የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶክተር ዐቢይ አህመድ በሁርሶ ሰላም ማስከበር ኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ተገኝተው የድህረ ምረቃ ዕጩ መኮንኖችን በማስመረቅ ላይ ናቸው።

ዕጩ መኮንኖቹ በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር  የትምህርትና ስልጠና ዋና መመሪያ ስር የሚገኘው የኢትዮጵያ ወታደራዊ  አካዳሚ ያሰለጠናቸው መሆናቸው ተገልጿል።

ለምረቃ የበቁት ዕጩ መኮንኖች በስልጠና ቆይታቸው ዘመናዊ ወታደራዊ ሳይንስና የአመራር ጥበብ  በንድፍ ሀሳብና በተግባር የተደገፈ ወታደራዊ የሙያ ትምህርት መከታተላቸውም ተመልክቷል።

 



 

በአሁኑ ወቅት ተመራቂዎቹ ትርኢት እያቀረቡ  ይገኛሉ።

በምርቃት መርሐግብሩ ላይ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀነራል ይልማ መርዳሳ፣ ከፍተኛ መኮንኖችና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም