ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሙስሊም ደንበኞቹና የቢዝነስ አጋሮቹ የረመዳን ኢፍጣር ማዕድ አጋራ

አዲስ አበባ መጋቢት 29/2015(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሙስሊም ደንበኞቹና የቢዝነስ አጋሮቹ የረመዳን ኢፍጣር ማዕድ አጋራ።

በመርሐ-ግብሩ ላይ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ፣ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰውና የማኔጅመንት አባላት እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው ሚኒስትሮችና የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ታዋቂ ግለሰቦች ተሳታፊ ሆነዋል።


 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ የረመዳን ጾም ሕዝበ ሙስሊሙ ከወዳጅ ዘመዱ ጋር በመሰባሰብ የሚረዳዳበትና በሕብረት የሚቆምበት ነው።  

ይህንንም ተከትሎ አየር መንገዱ የአብሮነትና የአንድነት ጊዜ ለማሳለፍ የኢፍጣር መርሐ-ግብር ለደንበኞቹ ማዘጋጀቱን አመልክተዋል። 


 

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሼኽ ሃጂ ኢብራሂም ቱፋ በበኩላቸው አየር መንገዱ በረመዳን ጾም የኢፍጣር መርሐ-ግብር በማዘጋጀቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በዚህ የጾም ወቅት ወንድማማቾች በመረዳዳት በጋራ የሚቆሙበት ወቅት በመሆኑ መሰል ተግባራት ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም