በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐሙድ አሊ የሱፍ ጋር ተወያየ - ኢዜአ አማርኛ
በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐሙድ አሊ የሱፍ ጋር ተወያየ
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ):- በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የተመራ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከጅቡቲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር መሐሙድ አሊ የሱፍ ጋር ውይይት አድርጓል።
ውይይቱ የሁለትዮሽና ቀጣናዊ ትብብሮች ላይ ያተኮረ መሆኑን በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡
በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ የተመራ የኢትዮጵያ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ትናንት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ መግባቱ ይታወቃል፡፡