ስምንተኛው የውሃ፣የውሃ ዲፕሎማሲና ኮሙኒኬሽን ፎረም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ይካሄዳል - ኢዜአ አማርኛ
ስምንተኛው የውሃ፣የውሃ ዲፕሎማሲና ኮሙኒኬሽን ፎረም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ይካሄዳል
አዲስ አበባ መጋቢት 28/2015(ኢዜአ)፦ ስምንተኛው የውሃ፣የውሃ ዲፕሎማሲና ኮሙኒኬሽን ፎረም ነገ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እንደሚካሄድ ተገለጸ።
ፎረሙ “ጠንካራ ዲፕሎማሲና ተግባቦት ለዘላቂ የውሃ ሀብት ልማት” በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።
የውሃና ኢኒርጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮችና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በፎረሙ ላይ ይሳተፋሉ።
የመጀመሪያው የውሃ፣የውሃ ዲፕሎማሲና ኮሙኒኬሽን ፎረም ላይ የቀረቡ ጥናትና ምርምሮችና መረጃዎችን ያካተተ ህትመት በይፋ እንደሚመረቅም ኢዜአ ከውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘው መረጃ ያመለክታል።
ሰባተኛው የውሃ፣የውሃ ዲፕሎማሲና ኮሙኒኬሽን ፎረም በታህሳስ 2015 በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መካሄዱ የሚታወስ ነው።
አምስተኛው ፎረም በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም በአርባምንጭ ከተማ በተካሄደበት ወቅት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር፣የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና መገናኛ ብዙሃንን ያካተተ የኢትዮጵያ የውሃ፣ የውሃ ዲፕሎማሲና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መማክርት ፎረም መመስረቱ ይታወቃል።
መማክርት ፎረሙ በግድቦች እና ውሃ ሀብት አስተዳደር ጉዳዮች ሙያዊ ድጋፍ መስጠት፣ዘርፉን የሚያሳድጉ ሳይንሳዊ ምክረ ሀሳቦችን ማቅረብና የሰራቸውን ውጤቶች በመገናኛ ብዙሃን የማሰራጨት ተግባር የሚያከናውን ነው።