ቀጥታ፡

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የልዑካን ቡድን ለስራ ጉብኝት ጅቡቲ ገባ

አዲስ አበባ መጋቢት 27/2015(ኢዜአ)፦ በብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የተመራ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ጅቡቲ ገብቷል።


 

ቡድኑ ጅቡቲ ሲደርስ በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬ አቀባበል አድርገዋል።

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የልዑካን ቡድን ትላንት በሶማሊያ በነበረው ቆይታ ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼህ መሐመድና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ማድረጋቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም