ቀጥታ፡

በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ መሀመድ ጋር ተወያየ

አዲስ አበባ መጋቢት 27/2015(ኢዜአ)፦በአቶ አደም ፋራህ የተመራ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ከሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ መሀመድ ጋር ውጤታማ ውይይት ማድረጉ ተገለጸ።


 

በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አደም ፋራህ የተመራና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ምስጋኑ አርጋ የሚገኙበት የልኡካን ቡድን በሶማሊያ የስራ ጉብኝት አድርጓል።

በጉብኝቱ ላይም ልዑካን ቡድኑ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከ መልዕክት ለሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐመድ ማድረሱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አመልክቷል።


 

ቡድኑ ከሶማሊያው ፕሬዝዳንት ጋር ፍሬያማ ውይይት ማድረጉም ተገልጿል።

ኢትዮጵያና ሶማሊያ በሁለትዮሽና ቀጣናዊ ትብብር የጋራ ፍላጎታቸው በሆኑ ጉዳዮች ላይ መምከራቸው ተጠቁሟል።

በብልፅግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አደም ፋራህ የተመራና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋን ያካተተው የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በሶማሊያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ትላንት ሞቃዲሾ መግባቱ ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም