የኢትዮ - አንጎላን ግንኙነት ማጠናከር ያስፈልጋል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮ - አንጎላን ግንኙነት ማጠናከር ያስፈልጋል - ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
አዲስ አበባ መጋቢት 26/2015 (ኢዜአ)፡-ለብዙ አመታት የዘለቀውን የኢትዮ - አንጎላ ወዳጅነት በቢዝነስ ዘርፉም ማጠናከር እንደሚገባ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ገለፁ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ የስራ ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን በኢትዮጵያ የአንጎላ አምባሳደር ፉራንሲስክ ጆስ ዲክሩዝ ባሰናበቱበት ወቅት የሁለቱ አገራት ወዳጅነት እንዲጠናከር ላደረጉት አስተዋጽኦ አመስግነዋል ።
የኢትዮ- አንጎላ ግንኘነት ከተለመደው የፖለቲካ ባሻገር በቢዝነስና እና ኢንቨስትመንት የማደግ እድሉ እንዳለ ገልፀዋል።
ተሰናባቹ አምባሳደር በበኩላቸው የኢትዮጵያ ባለሀብቶች በአንጎላ ለመሰማራት ፍላጎት እያሳዩ እንደሆነ ተናግረዋል ።