ኢትዮጵያ፣ከአውሮፓ ሕብረት እና ፈረንሳይ ጋር የ32 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ፣ከአውሮፓ ሕብረት እና ፈረንሳይ ጋር የ32 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ተፈራረመች
አዲስ አበባ፡ መጋቢት 25/2015(ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ፣ከአውሮፓ ሕብረትና ፈረንሳይ ጋር የ32 ሚሊዮን ዩሮ የድጋፍ ስምምነት ዛሬ ተፈራርማለች።
ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሬታ ሰዋሰው፣ የፈረንሳይ የልማት ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ቫለሪ ቴሂዮና በኢትዮጵያ የአውሮፓ ሕብረት ልዑክ የትብብር ኃላፊ ስቴፋን ሎክ ተፈራርመዋል።
ድጋፉ በግጭት አካባቢ የተጎዱ አካባቢዎች ተግባራዊ ለሚሆነው የምግብ ዋስትና ፕሮጀክትና የግብርና መልሶ ማገገም ስራዎች እንደሚውል የገንዘብ ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰፈረው መረጃ ገልጿል።
የፈረንሳይ ልማት ኤጀንሲ 18 ሚሊዮን ዩሮ እንዲሁም የአውሮፓ ሕብረት 14 ሚሊዮን ድጋፉን እንደሚያደርግ አመልክቷል።
ፕሮጀክቱ በግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢኒስቲትዩት እንደሚተገበርም ተጠቁሟል።