የኤርትራ የጦር ጀነራሎችና ከፍተኛ መኮንኖች የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
የኤርትራ የጦር ጀነራሎችና ከፍተኛ መኮንኖች የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ
አዲስ አበባ መጋቢት 25/2015 (ኢዜአ)፦ የኤርትራ መከላከያ ሰራዊት የጦር ጀነራሎች እና ከፍተኛ የጦር አመራር መኮንኖች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ።
የአመራር ቡድኑ የኢንስቲትዩቱን የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማት ዓቅም እና እየተከናወኑ ያሉ የምርምርና ልማት ስራዎችን ጎብኝቷል።
የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ወርቁ ጋቸና ኢንስቲትዩቱ እያከናወናቸው ባሉ የማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳቸው የጎሉ የምርምር እና ልማት ስራዎች ዙሪያ ለቡድኑ አባላት ገለጻ አድርገዋል።
የኤርትራ የጦር ጀነራሎች እና ከፍተኛ የጦሩ አመራሮች ቡድን አስተባባሪ ጀነራል አብርሃ ካሳ በኢንስቲትዩቱ ያደረጉት ጉብኝት ለሀገራቸው ብዙ ልምድ የቀሰሙበት መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በቴክኖሎጂው ዘርፍም አብረው መስራት የሚያስችላቸው እድል ስለመኖሩም የተገነዘቡበት ጉብኝት መሆኑን መናገራቸውን ከኢንስቲትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።