በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ - ኢዜአ አማርኛ
በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ይደረጋሉ
አዲስ አበባ መጋቢት 24/2015 (ኢዜአ)፦ በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 17ኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ-ግብር ዛሬ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ይከናወናሉ።
ከቀኑ 9 ሰዓት ፋሲል ከነማ ከወላይታ ዲቻ ይጫወታሉ።
በፕሪሚየር ሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ፋሲል ከነማ በ21 ነጥብ 10ኛ እንዲሁም ወላይታ ዲቻ በ22 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
በሌላኛው መርሐግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮ ኤሌትሪክ ጋር ከምሽቱ 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
ፈረሰኞቹ በ35 ነጥብ የሊጉ አናት ላይ የሚገኙ ሲሆን በአንጻሩ ኢትዮ ኤሌትሪክ በስምንት ነጥብ 15ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።
በተያያዘ ዜና ትናንት በተደረጉ 17ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታዎች አዳማ ከተማ መቻልን 3 ለ 2 እንዲሁም ሀዲያ ሆሳዕና ሲዳማ ቡናን 1ለ 0 አሸንፈዋል ።