ቀጥታ፡

መጋቢት 24 በሀገራችን የለውጥ መሰረት የተጣለበት ዕለት ነው--ከንቲባ አዳነች አቤቤ 


መጋቢት 24/2015(ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ መጋቢት 24 በሀገራችን የለውጥ መሰረት የተጣለበት ዕለት መሆኑን ገለጹ።

“ለዚህም አዲስ አበባችን ምስክር ናት ፤በብዙ ፈተናዎች ዉስጥ እመርታዎችን ማሳየት ችለናል” ሲሉም ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

ዛሬም ፈተናዎች ቢበዙብንም የህዝብን አመኔታ መቼም  ቢሆን አንዘነጋም፤ ክብራችን ህዝብን በፍትሃዊነት ማገልገል ስለሆነ ብለዋል።

ከንቲባ አዳነች አያይዘውም “ጊዜያዊ ፈተናዎችን ሁሉ ተሻግረን የኢትዮጵያ ብልጽግና እና የህዝቦቿ አንድነት እንደሚረጋገጥ የፀና እምነት አለን፣ መጪው ጊዜ ብሩህ ነው ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም