ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ተመሰረተ

አዲስ አበባ መጋቢት 24/2015 (ኢዜአ)፦  የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ተመሰረተ።

የምክር ቤቱ የምስረታ መርሃ -ግብር ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

የምክር ቤቱ ምስረታ ዋነኛ ዓላማ ወጣቶች ሰላማዊ ሞጋች፣ ጠያቂና ለአገር እድገት የላቀ አስተዋጽኦ እንዲኖራቸው ለማስቻል መሆኑ በመርሃ ግብሩ ላይ ተነስቷል።

በተጨማሪም ፓን-አፍሪካኒዝምን በተግባር ለማሳየትና ለቀጣናውም ጭምር ተምሳሌት የመሆን እቅድ ያነገበ መሆኑ ተመላክቷል።

በምክር ቤቱ የመመስረቻ መርሃ ግብር ላይ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚኒስትር ዶክተር አለሙ ስሜ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎችና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

"የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ለወጣቶች ድምጽ" በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ባለው ሁነት ከሁሉም የአገሪቷ አካባቢዎች የተውጣጡ ወጣቶች ታድመዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም