16ኛው የስልጤ ብሔረሰብ የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ሲምፖዝየም በወራቤ ከተማ እየተካሄደ ነው

ወራቤ መጋቢት 23/2015 ዓ.ም (ኢዜአ) 16ኛው የስልጤ ብሔረሰብ የባህል፣ የታሪክና የቋንቋ ሲምፖዝየም  በወራቤ ከተማ በመካሄድ ላይ ነው።

ለሁለት ቀናት የሚቆየው ሲምፖዚየም  ዓላማ የስልጤ ብሔረሰብ ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክና ባህላዊ እሴት አስጠብቆ በማስቀጠል ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ ግብ ያደረገ መሆኑ ተገልጿል።

በስነ ስርዓቱ ላይ የስልጤ ዞን አስተዳደር ከ410 ሚሊዮን ብር በላይ ለሚገነባው ባለ አምስት ወለል የአስተዳደር ሕንጻ የመሰረተ ድንጋይ ማኖር መርሐግብር ተከናውኗል።

የሕንጻ ግንባታው በሁለት ዓመታት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተጠቁሟል።

በስነሥርዓቱ ላይ የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰማን ሽፋ፣ የክልሉ እንሰሳትና ዓሳ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘይኔ ቢልካ፣ የስልጤ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ዓሊ ከድርን ጨምሮ ሌሎች አመራሮችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም