የሀገር ሠላም በአስተማማኝ መሠረት ላይ ጸንቶ እንዲቀጥል ሠራዊቱ ሚናውን አጠናክሮ ይቀጥላል- ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ

403

አርባምንጭ መጋቢት 23/2015(ኢዜአ)፦የሀገር ሠላም በአስተማማኝ ጠንካራ መሠረት ጸንቶ እንዲቀጥል ሠራዊቱ ሚናውን በበለጠ አጠናክሮ እንደሚቀጥል የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ገለጹ።

መከላከያ ሚኒስቴር በጋሞ ዞን ምዕራብ ዓባያ ወረዳ ያስገነባው ዘመናዊ አገልግሎቶችን ያካተተ የኮርና ሻለቃ መምሪያ ካምፕ ዛሬ ተመርቋል።


 

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት እንዳሉት በተለያየ መልኩ የሀገርን ሠላም ለመናድ የሚደረጉ ፍላጎቶች አሉ።

የሀገር ሠላም በጠንካራ መሠረት ላይ ታንፆ እንዲቆም ሠራዊቱ ኃላፊነቱን በበለጠ ብቃት እንደሚወጣም ገልጸዋል።

ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ የተገኘውን ሠላም ማጠናከር እንደሚገባ ገልጸው፤ ይሔንን ለማጽናትም ሠራዊቱ እየከፈለ ያለው መስዕዋትነት ሊደገፍ ይገባል ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

ሠራዊቱ ተልዕኮውን በበለጠ ብቃት እንዲወጣ የሚደረጉ ሁለንተናዊ የግንባታ ሥራዎችም በልዩ ትኩረት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም