ሁለተኛ ዙር የደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ወንዶች ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ በባህርዳር ከተማ ተጀመረ

አዲስ አበባ መጋቢት 23/2015 (ኢዜአ)፦ ሁለተኛ ዙር የደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ወንዶች ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ በባህር ዳር ከተማ ዛሬ ተጀምሯል።

በባህር ዳር ሚሊኒየም ሜዳ ከቀትር በፊት የስምንተኛ ሳምንት ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል።


 

ባህር ዳር ከተማ ብሔራዊ አልኮልን 3 ለ 2 እንዲሁም ሙገር ሲሚንቶ መቻልን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

በስምንተኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ይጫወታሉ።

የፕሪሚየር ሊጉ ከ8ኛ እስከ 11ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከመጋቢት 23 እስከ 29/2015 በባህር ዳር ከተማ እንደሚካሄዱ የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን አስታውቋል።


 

ከ12ኛ ሳምንት እስከ 14ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ደግሞ በአዲስ አበባ በማካሄድ ውድድሩን ለማጠናቀቅ መታቀዱንም ፌዴሬሽኑ አስታውቋል።


 

ከአንደኛ እስከ ሰባተኛ የነበሩት የውድድር መርሐ-ግብሮች በወላይታ ሶዶና ሮቤ ከተሞች መካሄዳቸው የሚታወስ ነው።

በደርባ ሚድሮክ ሲሚንቶ ወንዶች ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ስምንት ክለቦች ተሳታፊ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም