የወርልድ ቴኳንዶ ዓለም አቀፍ የዳኝነት የአሰልጣኞች ስልጠና መሰጠት ተጀመረ--የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር

341

አዲስ አበባ መጋቢት 23/2015 (ኢዜአ) የወርልድ ቴኳንዶ ዓለም አቀፍ የዳኝነት የአሰልጣኞች ስልጠና ዛሬ በአዲስ አበባ መሰጠት መጀመሩን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተዘጋጀው ይህ ስልጠና የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ከዓለም አቀፉ የወርልድ ቴኳንዶ ጋር በመተባበር መሆኑ ተገልጿል።


 

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የዓለም አቀፉ የወርልድ ቴኳንዶ ሊቀ-መንበር ጁንግ ሲዮክ ዮ፣ የዓለም አቀፍ ወርልድ ቴኳንዶ የዳኞች ሊቀ-መንበር አማን ሞራስ፣ የኢትዮጵያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ዳዊት አስፋው እንዲሁም የፌዴሬሽኑ ስራ አስፈጻሚ አባላት ተገኝተዋል፡፡


 

ስልጠናው በንድፈ ሃሳብና በተግባር የተደገፈ ሲሆን ከሳዑዲ አረቢያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ከኮትዲቯር፣ ከሩዋንዳና ኢትዮጵያ የመጡ ሰልጣኞች ይሳተፉበታል፡፡


 

ስልጠናውን አጠናቀው የሚሰጠውን ፈተና ያለፉ ሰልጣኞች የዓለም አቀፍ የቴኳንዶ ዳኝነት ሰርተፊኬት እንደሚሰጣቸው የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ ያወጣው መረጃ ያመላክታል።

ዓለም አቀፍ የቴኳንዶ የዳኝነት የአሰልጣኞች ስልጠናው እስከ መጋቢት 26/2015 . ድረስ እንደሚቆይ ተገልጿል

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም