መከላከያ ሚኒስቴር በጋሞ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ ለደቡብ ዕዝ የሰራውን የጦር መምሪያ የሻለቃ መኖሪያና መስሪያ ካምፕ እያስመረቀ ነው

184

አርባ ምንጭ መጋቢት 23/2015(ኢዜአ)፦ መከላከያ ሚኒስቴር በጋሞ ዞን ምዕራብ አባያ ወረዳ ለደቡብ ዕዝ የሰራውን የጦር መምሪያ የሻለቃ መኖሪያና መስሪያ ካምፕ በማስመረቅ ላይ ይገኛል።

በምረቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላን ጨምሮ የሚኒስቴሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ጀነራል መኮንኖች፣ የጋሞ የአገር ሽማግሌዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።


 

ዘመናዊ ካምፑ የኮር ጠቅላይ መምሪያና የሬጅመንት ጠቅላይ ሠፈር በርካታ ዘመናዊ አገልግሎት የሚሰጡ ግንባታዎች ያካተተ መሆኑን የግንባታው ፕሮጀክት ኃላፊ ሌተናል ኮሎኔል ዳኛቸው ያዴታ ለኢዜአ ገልጸዋል።

ካምፑ የውስጥ ለውስጥ መንገድ፣ ሆስፒታልና የንጹህ መጠጥ ውሃ ግንባታ እንዲሁም የመሰብሰቢያ፣ የመመገቢያ አዳራሾችና የመዝናኛ ማዕከላት መያዙን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም