የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን እያስመዝገበ ያለውን ለውጥና ትጋት አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል

129

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 23/2015 (ኢዜአ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትርና የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ወይዘሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ፣ ኮርፖሬሽኑ እያስመዝገበ ያለውን ለውጥና ትጋት አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አሳሰቡ።

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል የተቋሙን የሥራ እንቅስቃሴ ጨምሮ ኮርፖሬሽኑ በአጭር ጊዜ ግንባታዎችን ማጠናቀቅ ስለቻለበት የፕሮጀክት አስተዳደር ሥርዓት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡


 

ሚኒስትሯ ወይዘሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ፣ ከኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል ጋር በመሆን የተቋሙን የመስክ ሥራዎች ጐብኝተዋል፡፡

በዚሁም ወቅት አመራሩና ሠራተኛው በተገኘው ስኬት ሳይዘናጋ እያስመዘገበ ያለውን ለውጥ እንዲያጠናክርና ለላቀ ለውጥና ውጤት እንዲተጋ አሣስበዋል፡፡

የካቢኔ ሚኒስትሯ ወይዘሮ አለምፀሃይ፣ ተቋሙ በዋናው መስሪያ ቤትና በቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ዘመናዊ ቴክኖሎጂን መሰረት አድርጎ እያቀረበ ያለውን አገልግሎትና የዲጂታላይዜሽን አሰራር ሥርዓት ዝርጋታ ያለበትን ደረጃም ተመልክተዋል፡፡


 

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ረሻድ ከማል የተቋሙን የሥራ እንቅስቃሴ ጨምሮ ኮርፖሬሽኑ በአጭር ጊዜ ግንባታዎችን ማጠናቀቅ ስለቻለበት የፕሮጀክት አስተዳደር ሥርዓት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በአጭር ግዜ ውስጥ ገንብቶ ለአገልግሎት ያበቃቸውን ዘመናዊ ሚክስድ አፓርትመንት ሕንጻዎች መመልከታቸውንና የኮርፖሬሽኑ ለውጥና የተቋም ግንባታ በጣም ጥሩ በሆነ ደረጃ እየተጓዘ መሆኑን ሚኒስትሯ መጠቆማቸውን ከኮርፖሬሽኑ ማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያስረዳል።

በጉብኝቱ የኮርፖሬሽኑ የማኔጅመንት አባላት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም