ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኮሞሮስ ኅብረት ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒን ተቀብለው አነጋገሩ - ኢዜአ አማርኛ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኮሞሮስ ኅብረት ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒን ተቀብለው አነጋገሩ

አዲስ አበባ መጋቢት 22/2015(ኢዜአ)፦ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የኮሞሮስ ኅብረት ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ "የኮሞሮስ ኅብረት ፕሬዝዳንት አዛሊ አሱማኒን ዛሬ በቢሮዬ ተቀብዬ በሁለትዮሽ፣ በክልላዊ እና በባለ ብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል" ሲሉ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።
ኢትዮጵያ ከኮሞሮስ ጋር ላላት ግንኙነት ትልቅ ቦታ ትሰጣለች፤ በተለያዩ መስኮች ያለውን ትብብር ለማጠናከርም ትሠራለች ብለዋል።