የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ስልጠና ማካሄድ ጀመሩ


አዲስ አበባ መጋቢት 22/2015(ኢዜአ)፦የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት "የተገኙ ድሎችን ማጽናትና ፈተናዎችን መሻገር" በሚል መሪ ሃሳብ ስልጠና ማካሔድ ጀምረዋል።

የስልጠናው ዋና አላማም ባለፉት ዓመታት የተመዘገቡ ድሎችን ለማጽናትና ፈተናዎችን በመሻገር የሕዝብ ጥያቄዎችን በበቂ ሁኔታ ለመመለስ ያለመ ነው።

ህገ-መንግስታዊ አሠራርን በመከተልና ሕዝባዊ ኃላፊነትን መወጣት በሚያስችልበት ሁኔታ መሠረት ተደርጎ የሚሰጥ መሆኑም ተገልጿል።

በዚህም የምክር ቤቱ አባላት በአመለካከት፣ በተግባርና በሥነ-ምግባር ግንባር ቀደም ሊሆኑ እንደሚገባና የፓርላሜንታዊ ስርዓቱ ጠንካራ ዲሲፕሊን በሚጠበቅበት ሁኔታ በቀጣይ እንደሚሠራ ተመልክቷል፡፡

ሥልጠናው አባላት በአመለካከት፣ በተግባርና በሥነ-ምግባር ግንባር ቀደም መሆን እንዲችሉ ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በመሆኑም የተገኙ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመለየት ስኬቶችን በማጽናት እንዲሁም ፈተናዎችን ለመሻገር የቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ሥልጠና እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ምክር ቤቱ ህብረ-ብሔራዊነትን መሠረት አድርጎ የተመሠረተ በመሆኑ አንድነትን ለማጽናት በትኩረት ይሠራል ተብሏል፡፡


ሥልጠናው ለቀጣይ ሦስት ቀናት የሚቀጥል መሆኑንም ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም