የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩት አቶ ፋንታሁን ደለለው ሽፈራውን ከስራ አሰናበተ

374

አዲስ አበባ መጋቢት 21/2015(ኢዜአ)፦ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩት አቶ ፋንታሁን ደለለው ሽፈራውን ከስራ ማሰናበቱን አስታወቀ።

ምክር ቤቱ 12ኛ መደበኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው።


 

በስብስባው ላይ በምክር ቤቱ የሕግና ፍትሕ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ እፀገነት መንግስቱ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኛ የነበሩት አቶ ፋንታሁን ደለለው ሽፈራውን የስራ ስንበት የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል።

አቶ ፋንታሁን የዳኞች የስነ-ምግባርና የዲሲፕሊን ክስ ስነ-ስርዓት ደንብ በመተላለፍና የሐቀኝነት ተነጻጻሪ ግዴታ በመተላለፍ ከአመልካች ብር 100ሺህ መደለያ መቀበላቸው በማስረጃ ተረጋግጧል ብለዋል።

ምክር ቤቱም የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ ሪፖርት ካዳመጠ በኋላ የአቶ ፋንታሁን ደለለው ሽፈራውን የስራ ስንብት የውሳኔ ሃሳብ ቁጥር 13/2015 አድርጎ በሙሉ ድምጽ ማጽደቁን ከሕዝብ ተወካዮች ምከር ቤት ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም