ቀጥታ፡

አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ጋር ተወያዩ

 

አዲስ አበባ መጋቢት 20/2015(ኢዜአ)፦በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው ከቻይና የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ዡ ቢንግ ጋር ተወያይተዋል።


 

ውይይታቸው የሁለትዮሽ እንዲሁም የቻይና-የአፍሪካ ቀንድ ግንኙትን ማጠናከር የሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነበር።

የስራ ሃላፊዎቹ በተለይ የቻይና አፍሪካ ቀንድ የግንኙነት ማዕቀፍ ትግበራን ለማጠናከር በቅርበት መስራት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት መስጠታቸውን በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም