መንግስት ኢትዮጵያን ማጽናት የሚያስችል የህግ አስከባሪ ተቋማትን ገንብቷል-ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

አዲስ አበባ መጋቢት 19/2015 (ኢዜአ)፦ መንግስት ኢትዮጵያን ማጽናት የሚያስችል የህግ አስከባሪ ተቋማትን መገንባቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

መንግስት ሀገርን ከመፍረስ ለመታደግ በርካታ ስራዎችን መስራቱን እና ከዚህ በኋላ “ሀገር ትፈርሳለች የሚል ስጋት የለንም“ ብለዋል።

ዲሞክራሲን ለመገንባት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ጥረት ከነችግሩም ቢሆን ማገዝ ተገቢ መሆኑን አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም