ከመራጩ ህብረተሰብ በተነሱ ጉዳዩች ላይ ከአስፈፃሚ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው - ኢዜአ አማርኛ
ከመራጩ ህብረተሰብ በተነሱ ጉዳዩች ላይ ከአስፈፃሚ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው

አዲስ አበባ መጋቢት 18/ 2015 (ኢዜአ) በኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከመራጩ ህብረተሰብ በተነሱ ጉዳዮች ላይ ከአስፈፃሚ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ መሆኑ ተገለጸ።
ምክር ቤቱ በዓመት ሁለት ጊዜ ከመረጠው ሕዝብ ጋር ውይይት የሚያደርግ መሆኑን ጠቅሰው፤ በዚህም በየካቲት ወር ባደረገው የሕዝብ ውክልና ስራ ከመራጩ ሕዝብ ጋር በተደረገ ውይይት የልማት፣ የመልካም አስተዳደር፣ የሠላም እና የኑሮ ውድነትን በተመለከተ ከመራጩ ሕዝብ የተነሱ ጥያቄዎችን ለሚመለከተው አስፈፃሚ አካላት መቅረቡ ተገልጿል።
ይህንኑ በተመለከተ የመንግስት ተጠሪ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ መሠረት ኃይሌ በየምርጫ ክልሉ የነበረው የውይይት ሂደት በተመለከተ ሪፖርት አቅርበው ውይይት እየተደረገ መሆኑን ከምክርቤቱ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡