የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያዩ

363

አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከከተማዋ ነዋሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን ገለጹ።


 

ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከከተማችን ነዋሪዎች ጋር ተወያይተናል” ብለዋል።


 

በውይይቱም “ስኬቶቻችንን አስጠብቀን፣ ጉልበት የሚሆኑ ገንቢ ሃሳቦች እና ሊታረሙ በሚገቡ እንዲሁም ትኩረት በሚፈልጉ ጉድለቶቻችን ላይ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል“ ሲሉም አክለዋል።


 

ከንቲባ አዳነች አቤቤ ከተማዋን የሚመጥን አስተሳሰብ ማሰረፅ፣ ፅንፈኝነት፣ ጥላቻንና ህዝብን የሚከፋፍሉ የሴራ ፖለቲካን በጋራ ለመከላከል መግባባት መደረሱን ገልጸዋል።


 

በተጨማሪም “የኑሮ ውድነት ጫናን መቀነስ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ነዋሪዎችን የሚደግፉ ፕሮጀክቶችን ማስፋፋት፣ እንዲሁም ከህዝባችን የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመቅረፍ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራበት መሆኑን ተግባብተናል” ሲሉም ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም