"የመደመር ትውልድ (Dhaloota Ida'amuu) መጽሐፍ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የማስተዋወቅ ስነ-ስርዓት ተካሄደ

177

ሐረር መጋቢት 17/2815 (ኢዜአ) በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው "የመደመር ትውልድ” (Dhaloota Ida'amuu) መጽሐፍ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን የማስተዋወቅና ሽያጭ መርሃ ግብር ተካሄደ።

የማስተዋወቅ መርሃግብሩ እየተካሄደው በሐረር ከተማ በሚገኘው የሐረሪ ክልል ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ነው።

በመርሃ ግብሩ ላይ የጨፌ ኦሮሚያ አፈ-ጉባኤ ሰዓዳ አብዱረህማንና የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ወይዘሮ ሚስኪ መሀመድን ጨምሮ የክልሉና የዞኑ ከፍተኛ  የስራ ሃላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ አባ ገዳዎች፣ ባለሀብቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

በክልሉ ከመጽሐፉ ሽያጭ የሚገኘው ገቢ በባሌ ዞን ለሚገኘው የሶፍ ዑመር ዋሻ የቱሪዝም መሠረተ ልማት ማስገንቢያ እንደሚውል ተገልጿል።

May be an image of book

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ የተጻፈው የ"መደመር ትውልድ" (Dhaloota Ida'amuu) መጽሐፍ በአፋን ኦሮሞ፣ በአማርኛ እና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን ሶስት ክፍሎች እና አስር ምዕራፎችም አሉት።

የ"መደመር ትውልድ" መጽሐፍ መጋቢት 9 ቀን 2015 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች በተገኙበት መመረቁ ይታወሳል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም