ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድርን አትሌት መዲና ኢሳ በአንደኝነት አጠናቀቀች - ኢዜአ አማርኛ
ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድርን አትሌት መዲና ኢሳ በአንደኝነት አጠናቀቀች

አዲስ አበባ መጋቢት 17/2015 (ኢዜአ)፦ የሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች የ5 ኪ.ሜ የሩጫ ውድድርን አትሌት መዲና ኢሳ በአንደኝነት አጠናቀቀች።
አትሌት መዲና ኢሳ በመሪነት በማጠናቀቋ የ70ሺህ ብር ተሸላሚ ስትሆን በተጨማሪም በውድድሩ አዲስ ክብረ-ወሰን በማስመዝገቧ የ50ሺህ ብር ሽልማት ተበርክቶላታል።
በውድድሩ አትሌት ፅጌ ገብረ ሰላማ 2ኛ እንዲሁም አትሌት መልክናት ውዱ 3ኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቃቸው እንደቅደም ተከተላቸው የ45ሺህ ብር እና የ30ሺህ ብር ተሸላሚ ሆነዋል።
በውድድሩ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ፣ ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረ ሥላሴ፣ አትሌት መሰረት ደፋር፣ አትሌት ለተሰንበት ግደይን ጨምሮ የተለያዩ አትሌቶችና እንግዶች ተገኝተዋል።
የ2015 ሳፋሪኮም ቅድሚያ ለሴቶች 5 ኪሎሜትር ሩጫ ”ቦታዬ፤ መብቴ፤ ድምፄ” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ባለው በዚህ ውድድር አትሌቶች፣ 15 ሺህ የጤና ሯጮች፤ እንዲሁም አምባሳደሮች እየተሳተፉ ነው።